አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
የክልሉ ምክር ቤት አቶ ተስፋዬ ይገዙን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል፡፡
እንዲሁም አቶ አለማየሁ ባውዲ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመንግስት ዋና ተጠሪ፣ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የውሃ ማዕድን ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ዮሐንስ በየነ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ፣ አቶ ዳዊት ገበየሁ የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ በማድረግ ምክር ቤቱ ሹመታቸውን አጽድቋል።
እንዲሁም አቶ ቦጋለ ፈይሳ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሾሙ አቶ አንዱአለም አምባዬ ደግሞ ምክትል የክልሉ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ተሹመዋል።
ሹመታቸው በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበውም ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በማቱሣላ ማቴዎስ