Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በነፋስ ኃይል የምትንቀሳቀስ እቃ መጫኛ መርከብ የመጀመሪያ ጉዞዋን ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታኒያውያን ዲዛይን የተደረገችው ልዩ የነፋስ ኃይል ሸራዎች የተገጠመላት ግዙፍ የጭነት መርከብ ለባህር ላይ ጉዞ ተዘጋጅታለች።

መርከቧ ግዙፍ የነፋስ ሸራዎችን በመጠቀም የምትንቀሳቀስ ሲሆን፥ አሁን ላይ የናረውን የነዳጅ ፍጆታ በመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና ይኖራታል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የካርበን ልቀትን በማስቀረት የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ያደርጋል መባሉን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

የእቃ ጫኝ መርከቧ ከቻይና ብራዚል የምትጓዝ ሲሆን ፥ የነፋስ-ክንፍ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።

የመርከቧ ክንፍ ወደብ ላይ ሲሆን የሚታጠፍ ሲሆን መርከቧ በምትንቀሳቀስበት ወቅት ደግሞ በመዘርጋት የመርከቧን ጉዞ ያፋጥናል ተብሏል።

ቁመታቸው 37 ነጥብ 5 ሜትር ሲሆን ፥ የነፋስ ኃይል ተርባይኖች በሚሰሩበት ተመሳሳይ ቁሳቁስ የተሰሩ መሆናቸውም ታውቋል።

የጭነት መርከብን በሞተሩ አማካኝነት ከመንቀሳቀስ ይልቅ የነፋስ ኃይልን መጠቀሙ 30 በመቶ የካርበን ልቀትን እንደሚቀንስ ታምኖበታል።

የመርከብ ኢንዱስትሪው በየዓመቱ የሚለቀውን 837 ሚሊየን ቶን ካርበን ለመቀነስ እየሞከረ በመሆኑ የነፋስ ሃይል ቴክኖሎጂን በስፋት ለመጠቀም የአሁኑ ጅማሮ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በዚህም የነፋስ ኃይል ቴክኖሎጂ የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያመጣ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑ ሲሞን ቡሎክ (ዶ/ር) ይገልጻሉ፡፡

አክለውም “አሁን እየተመለከትን ያለውን የአየር ንበረት ለውጥ አደጋን ለመቀነስ ብሎም ዓለም ስጋት እንዳይኖርባት ለማድረግ በተቻለ መጠን መርከቦች ከካርበን ልቀት ነጻ መሆን አለባቸው” ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

መርከቧን የተከራየው ካርጊል የባህር ላይ ትራንስፖርት ድርጅት ፥ ቴክኖሎጂው ኢንዱስትሪውን በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመምራት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ገልጿል።

#windpoweredcargoship #zerocarbon

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ሰግናለን!

Exit mobile version