Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ያላትን ትብብር ለማጎልበት በትኩረት እንደምትሰራ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ትብብር ለማጠናከር በትኩረት እንደምትሰራ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እፀገነት በዛብህ ገለጹ።

አምባሳደር እፀገነት ፥ የሹመት ደብዳቤያቸውን እና ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የተላከ የመልካም ምኞት መልዕክትን ለዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ያላት ግንኙነት ስትራቴጂካዊ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ÷ ሀገራቱ ያላቸውን የዳበረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ እንዲያጠናክሩ፣ የሕዝብ ለሕዝብ እንዲሁም የኢኮኖሚ ግንኙነቱን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሀገራቱ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በቅርበት እየሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር እፀገነት በዩጋንዳ የተሳካ የስራ ቆይታ እንዲኖራቸውም ፕሬዚዳንቱ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#Ethiopia #Uganda

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version