አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተፈፅመዋል ያላቸውን የ752 ሕገ-ወጥ የሠራተኛ ቅጥር ሰረዝኩኝ አለ።
የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኃይሉ ሀሰና በሰጡት መግለጫ÷ በክልሉ በመንግስት ተቋማት የሚፈጸም የስራ ቅጥር፣ ዝውውርና የደረጃ እድገቶችን ተከትሎ በሚቀርቡ ጥቆማዎችና ኦዲት በማድረግ በሚያገኛቸው መረጃዎች መሰረት የእርምት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመትም በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተፈጸመ የ752 ሕገ-ወጥ የሠራተኛ ቅጥር መሰረዙን ነው የገለጹት፡፡
ኃላፊው ከሕገ-ወጥ ቅጥሮች መካከል በሐዋሳው አዳሬ ሆስፒታል የተፈጸመው 9 ሜዲካል ዶክተሮችን ጨምሮ የ19 የፋርማሲና ላብራቶሪ ቴክኒሻን ባለሙያዎች ቅጥሩን ህገወጥ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
ነገር ግን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ማጣራት እና ባከናወነው ምርመራ ይህ ቅጥር ህጋዊ መንገዱን ተከተሎ የተፈፀመ መሆኑን አረጋግጧል።
በምርመራ ስራው የተሰበሰቡት ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ቅጥር ህጋዊ ሆኖ ሳለ አለአግባብ “ህገወጥ” በሚል ተሰርዟል።
አሁን መግለጫ የሰጡት የስራ ሃላፊም በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ሀላፊ ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!