አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በዓለም ጤና ድርጅት በኩል ያገኘውን 28 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎች ለተለያዩ የሕክምና ተቋማት አበረከተ፡፡
ድጋፉ ለእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ የሕክምና መርጃ መሳሪያዎችን ያካተተ ሲሆን÷ በጅማ ከተማ ፣ ጅማ ዞን፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አምቦ ከተማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ የግብዓት እጥረት ላለባቸው የጤና ተቋማት ተበርክቷል፡፡
ለሕክምና ቁሳቁሱ መግዣነት የዋለው 28 ሚሊየን ብር ከካናዳ የውጭ ጉዳይ የተገኘ ሲሆን÷ በዓለም ጤና ድርጅት በኩል ነው ለዩኒቨርሲቲው የተላለፈው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር)÷ ዩኒቨርሲቲው በማሕበረሰብ አቀፍ ፍልስፍናው እየተመራ ሕብረተሰቡን ማዕከል ያደረጉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡
ለጤና ተቋማቱ የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም ዩኒቨርሲቲው ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ተጠቅሞ ለሕበረተሰቡ ጤና መሻሻል እየሰራ መሆኑን ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በወርቃአፈራሁ ያለው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!