Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በባሕርዳር ከተማ አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ ላይ እደሚወያይ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጉባዔው ከላይ በተገለጸው አጀንዳ ላይ ከተወያያ በኋላም ችግሮች በዘላቂነት ስለሚፈቱበት ሁኔታ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version