አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አጋጣሚዎች የእሳት ቃጠሎ ሊያጋጥም ይችላል።
በዚህ ምክንያትም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።
በሰውነት ላይ የእሳት ቃጠሎ ሲያጋጥም ማድረግ ያለብን እና የሌለብን ነገሮች ምንድናቸው?
በእሳት የተቃጠለውን ቦታ በውሃ ማቀዝቀዝ፣ ንፁህ እና ደረቅ ጨርቅ በተቃጠለው ቦታ ማድረግ፣ ያደረግናቸው ጌጣጌጦች ካሉ ማውለቅ እና ወደህክምና ተቋም መሄድ በእሳት ቃጠሎ ወቅት መወሰድ ያለበት እርምጃ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መረጃ ያመላክታል፡፡
በጣም የቀዘቀዘ ወይም በረዶ በተቃጠለው ቆዳ ላይ ማድረግ፣ እንደ ቅባት ያሉ የተለያዩ ነገሮችን መጠቀም በቃጠሎው ቆዳችን ላይ የተጣበቀውን ልብስ ለማንሳት መሞከር እና በቃጠሎው ውሃ የቋጠረውን የቆዳ ክፍል ለማፍረጥ መሞከር ደግሞ በዚህ ወቅት አይመከርም።