አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት በሕገ-ወጥ ግብይት ላይ ተሰማርተው በተገኙ 395 ሺህ 154 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
እርምጃው በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በመሰረታዊ የንግድ እቃዎች ግብይት ላይ በተደረገ የቁጥጥር ስራ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ነጋዴዎቹ ምርት በመከዘን፣ ያለ ንግድ ፈቃድ በመነገድ፣ ያለ ደረሰኝ ግብይት በመፈፀም፣ በሲሚንቶና ነዳጅ ስርጭት ሕገ-ወጥ ንግድ ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደተገኙ ተጠቁሟል፡፡
የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ ሕገ ወጥ ንግድ ቤቶችን ማሸግ፣ መሰረዝ እና የማግድ ተግባራትም በሕገ ወጥ ነጋዴዎቹ ላይ የተሰወዱ እርምጃዎች ናቸው፡፡
በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናክር በመሰረታዊ እቃዎች ግብይት ላይ የሚደረገው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡