አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለምአቀፉ የኃይል አቅርቦት ገበያ በቅርቡ በ”ብሪክስ” አባል ሀገራት ቁጥጥር ሥር እንደሚውል በዘርፉ የወጣ ጥናት አመላከተ፡፡
ቡድኑ በቅርቡ ግማሽ ያኅሉን የዓለም የነዳጅ ዘይት አቅርቦት እንደሚቆጣጠርም ኢንፎ ቴክ በፈረንጆቹ 2022 ያወጣውን የነዳጅ ዘይት አምራቾች እና ላኪ ሀገራት የቁጥር መረጃ ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል፡፡
ቡድኑ አሁን ጥያቄያቸውን የተቀበላቸውን ሥድስት ሀገራት በቋሚነት ካካተተ የዓለማችንን ግማሽ ያኅል የነዳጅ ዘይት ምርት እና ክምችት መቆጣጠር እንደሚያስችለውም ተጠቁሟል፡፡
ሀገራቱ በፈረንጆቹ 2024 ቋሚ አባል ሲሆኑ ከመሥራቾቹ ጋር ተደምረው የዓለማችንን 39 በመቶ ያኅል የነዳጅ ዘይት ወጪ ንግድ መቆጣጠር እንደሚያስችላቸው እና የዓለማችን 47 ነጥብ 6 በመቶ ያኅሉ የነዳጅ ዘይት በሀገራቱ እንደሚመረት ተገልጿል፡፡
በቅርቡ የአባልነት ጥያቄ ያቀረበችው ቬኔዙዌላ ተቀባይነት ካገኘች ደግሞ የአባል ሀገራቱን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እንደሚያልቀው እና የአባል ሀገራቱ የነዳጅ ክምችት የዓለማችንን 65 ነጥብ 4 በመቶ አካባቢ እንደሚያኅልም ተነግሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!