Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡

መድረኩ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ዘሀራ ሁመድ ፥ ረቂቅ አዋጁ “አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመፍጠር” ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በዚህም በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መካከል የጋራ መግባባት መፍጠር ቀዳሚ አጀንዳ ተደርጎ በመወሰዱ ቋሚ ኮሚቴው መድረክ እንዲዘጋጅ ማድረጉንም ነው የተናገሩት፡፡

ለአዋጅ ተፈፃሚነትም ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተሥፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ አዋጁ መቀረጹ ወጣቶች በልማት፣ በሠላምና ደኅንነት አስተዋፅዖ በማበርከት ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ እንደሚያስችልም ነው የተለጹት፡፡

መንግስት አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት አድርጎም የግንዛቤና የውይይት መድረኮችን እንዲፈጥርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዘርግቶ አገልግሎቱን እንዲተገብር ጠይቀዋል፡፡

ብሔራዊ የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት አዋጅ አምሥት ዋናዋና ክፍሎች ሲኖሩት ፥ አዋጁን ለማስፈፀም የሚወጡ ደንቦችን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ከአዋጁ መፅደቅ በኋላ መመሪያዎችን ሊያወጣ እንደሚችል ተጠቅሷል።

በምክክሩ ከመድረኩ የተለያዩ ግብዓቶችና አስተያየቶች የተሰበሰቡ ሲሆን ፥ ቀጣይ አቅጣጫ በመጠቆም መጠናቀቁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version