Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ውጤታማነት እየተሰራ ነው- ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ እውቀትንና ክህሎትን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ ለዘርፉ ወጤታማነት እየተሰራ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ክህሎትን እና እውቀትን የሚያገናኝ ድልድይ መሆኑን አንስተዋል።

ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል፡፡

የኢንስትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ተቋሙ የምርምር ክፍተቶችን እየሞላ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ተመራቂዎችም የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ለሀገር የቴክኖሎጂ እና የስራ ፈጠራ እድገት ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል እና የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ንጉሱ ጥላሁንን ጨምሮ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version