አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሳተፈው ልዑካን ቡድን ነገ አቀባበል እንደሚደረግ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ በሃንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያ ጥሩ ውጤት ያገኘችበት ነው ።
በውድድሩ ኢትዮጵያ 2 ወርቅ ፣ 4ብርና 3 ነሃስ ሜዳሊያዎች ማገኘቷን ጠቁመው ፥ ውጤቱ የኢትዮጵያን ገጽታ የገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተገኘው ውጤት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ሚኒስትሩ ፥ ለአትሌቲክስ ልዑኩ ነገ 23/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ጀምሮ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል እንደሚደረግም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያዊያንና ስፖርት አፍቃሪው ማህበረሰብ ነገ በሚደረገው አቀባበል ላይ በመገኘት የቡድኑን አባላት አንዲያበረታታም ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 2 ሰዓት የሚደረገውን አቀባበል ቀጥሎ አትሌቶቹ በአውራ ጎዳናዎች በመዘዋወር ከህዝቡ ጋር ደስታቸውን እንደሚገልጹም ተመልክቷል።
#Ethiopia #athletics #budapesthungary
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!