Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የልማት ግቦችን ለማሳካት መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከልማት አጋሮች ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች እና የልማት አጋሮችም እነዚህን ተግባራት በመደገፍ ረገድ በሚኖራቸው ሚና ላይ ያተኮረ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቧን የገለጹት ፍፁም (ዶ/ር÷ የልማት ግቦችን ለማሳካት መንግስት ከልማት አጋሮች ጋር በቅንጅት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አብራርተዋል።
የልማት አጋሮች ቡድን (ዲ ፒ ጂ) አዲሱ ተባባሪ ሊቀመንበር ራሚዝ አላክባርቮ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያ የመንግስትን ጥረት እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
ከአየር ንብረት ለውጥ ሥራ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 28) ላይ እንድትሳተፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትና የልማት ቡድኑ ትብብር በመጪዎቹ ዓመታት ፍሬያማ ሆኖ እንደሚቀጥል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 7 people, people studying and text
All reactions:

33

Exit mobile version