Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋቦን ወታደሩ የመንግስትን ስልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋቦን ወታደራዊ አመራሮች የመንግስትን ስልጣን መቆጣጠራቸውን በይፋ አስታወቁ።

የመንግስት ግልበጣው ከመካሄዱ ከደቂቃዎች በፊት የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን፥ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው 64 ነጥብ 27 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን መመረጣቸውን አሳውቆ ነበር።

ጋቦን24 በተሰኘው ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀረቡት 12 ከፍተኛ አመራሮች፥ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ በድጋሚ አሸንፈውበታል የተባለውን የምርጫ ውጤት መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የጋቦን ማዕከላዊ መንግስት፣ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት፣ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እና የሃገሪቱ ምርጫ ኮሚሽኑ በይፋ መፍረሳቸውን አውጀዋል።

አሁን ላይም የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ ‘በቤት ውስጥ እስር’ ላይ እንደሚገኙም ወታደራዊ አመራሮቹ መግለጻቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version