አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የጥናትና ምርምር ተቋማት ፎረም ዛሬ በይፋ ተመስርቷል።
ፎረሙ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፣ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና ሌሎች የጥናትና ምርምር ተቋማትን ያካተተ ነው።
በፎረሙ የተካቱት አስራ ሶስት ተቋማት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የፎረሙ ምስረታ ዋና ዓላማ በቀጣይ ኢትዮጵያ ለምታካሂዳቸው የልማት ዕቅዶች በተቀናጀ መልኩ በጥናትና ምርምር መደገፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ አማራጭ አቅጣጫዎችንና የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማመንጨት ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
እንዲሁም በምርምር ተቋማት መካከል ትብብር በማስፈን እውቀት መጋራትን ማመቻቸትና የምርምር ውጤቶችን ለማስፋት እንደሚያግዝ ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!