Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ከአውሮፓ ኅብረት ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

ውይይቱ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በምትከተለው የገንዘብ ፖሊሲ ላይ ያተኮረ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በባንኩ ዘርፍ እና በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ መምከራቸው ተመላክቷል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ÷ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ሪፎርሙ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ሥራ ላይ የተሠማሩ የውጭ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን እንደሚያበረታታም አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ የባንክ እና ኢንቨስትመንቱ ዘርፍ እየተጠና አሥፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን ለማድረግ በመንግሥት በኩል ቁርጠኝነት መኖሩን አብራርተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version