Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጆሃንስበርግ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ህንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

በአደጋው ከ40 በላይ ሰዎችም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተገለጸ ሲሆን በከተማዋ መሀል የሚገኝ ህንፃ መውደሙ ነው የተገለፀው፡፡

የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው÷ አደጋው በባለ 5 ፎቅ ህንፃ ላይ የተከሰተ ሲሆን የአደጋው ምክንያት በግልፅ አልታወቀም፡፡

የእሳት አደጋ ሰራተኞች በህንፃው ላይ የሚገኙ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደ ህክምና ቦታ የመውሰድና ተጨማሪ የሞቱ ሰዎችን የመፈለግ ስራቸውን ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

የእሳት አደጋ በደረሰበት ህንፃ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞች ይኖሩበት እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

Exit mobile version