Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

15 ኪሎ ግራም ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 6 ዳትሰን ሰፈር ተብሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ጠጅ ቤት 15 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ በወረቀት በመጠቅለል 87 ጥቅል ይዞ ለተጠቃሚዎች ለመሸጥ ጠጅ ቤቱ በር ላይ በራስ ደስታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

አደንዛዥ ዕፅ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ጤና በማቃወስ ህልማቸውን የሚያመክን ከመሆኑም ባሻገር ለወንጀል መንስኤ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል፡፡

ስለሆነም የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ፖሊስ የሚያከናውነውን ተግባር በመደገፍ ህብረተሰቡ መረጃ እና ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡

Exit mobile version