Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኳታር በኢትዮጵያ በምታስገነባው ልዩ የኩላሊት ሕክምና ሆስፒታል ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከኳታር የልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ኸሊፋ ብን ጃስም አልከዋሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ እና በኳታር የሁለትዮሽ ትበብር ማዕቀፎች ዙሪያ መምከራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ በለፈም ኳታር በኢትዮጵያ ለመገንባት ባቀደችው ልዩ የኩላሊት ሕክምና ሆስፒታል ቅድመ ዝግጅት እና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

Exit mobile version