አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቻይናዋ ቼንግዱ ከተማ-አዲስ አበባ የአውሮፕላን ጭነት አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በቼንግዱ ከተማ በተካሄደው የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮች፣ የቻይና የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ሀገራቱ የጭነት አገልግሎት ልማት ትብብር ስምምነት መፈራረማቸውንም በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡