አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 25ኛውን የትምህርት ጉባኤ እና የ2016 የትምህርት ዘመን ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) እና ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አመራር እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በጸጥታ ችግሩ ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነው የቆዩ 53 ሺህ ህጻናትን ጨምሮ በ2016 የትምህርት ዘመን 305 ሺህ 672 አዲስና መደበኛ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ያለመ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!