Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሚቀጥሉት አስር ቀናት በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየቀነሰ ይሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተዳከሙ የሚሄዱበት ጊዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዝናብ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየቀነሰ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዉ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በመካከለኛዉ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደግሞ የተሻለ ገጽታ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በእነዚህ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

በተጨማሪም በጸሀይ ሀይል ታግዛው ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version