Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የስምጥ ሸለቆ ሃይቆችን ለኢኮ ቱሪዝምና ለመስኖ ስራ ለማዋል በትብብር መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስምጥ ሸለቆ ሃይቆችን ለኢኮ ቱሪዝም፣ ለመስኖና ለመጠጥ አገልግሎት ለማዋል በትብብር መስራት እንደሚገባ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ የማዕከላዊ ስምጥ ሸለቆ ሃይቆችን በደንበል ሻላ ዙሪያ አሳታፊ በሆነ መልኩ ለማልማት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

በሚኒስቴሩ የውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) ÷ የውሃ ሃብትን በመጠንና በጥራት በመለየት ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል መመሪያ ተዘጋጅቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የስምጥ ሸለቆ ሃይቆችን ለኢኮ ቱሪዝም፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ እና ሌሎች አገልግሎቶች ለማዋል በትብብር መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በሃይቆች ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ከባለ ድርሻ አካላት እና ባለሃብቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት መመሪያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

የማዕከላዊ ስምጥ ሸለቆ እምቅ ሃብት ያለው በመሆኑ የመተግበሪያ እቅድ ወጥቶ በዘርፉ መጠቀም የሚችሉ አካላት መለየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በሃይቆቹ ላይ የተፈጠሩትን ተግዳሮቶች ወደ እድል በመቀየር ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥቅም እንዲያውሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version