አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ የሀሪቱን የመከላከያ ሚኒስትር አሌክሲ ሬዝኒኮቭን በአዲስ እንደሚተኩ አስታወቁ፡፡
ውሳኔያቸውን ለሀገሪቷ ምክር ቤት እንደሚያቀርቡም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው መናገራቸውን ዋን ኢንዲያ ዘግቧል፡፡
በምትካቸው የዩክሬን የንብረት ፈንድ ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙትን ሩስቴም ኡሜሮቭ እንደሚሾሙ ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንቱ÷ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስኩት መከላከያ ሚኒስቴሩ ከጦር ኃይሉ እና ከኅብረተሰቡ ጋር መሥተጋብር የሚፈጥርበት መንገድ በአዲስ አቀራረብ እና ቅርፅ መቀየር ስላለበት ነው ብለዋል።
ምክር ቤቱ ሐሳባቸውን ደግፎ ላቀረቡት ዕጩ ድጋፉን እንደሚሠጥ ያላቸውንም ዕምነት ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!