Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት አለበት- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

መቀመጫቸውን አርባ ምንጭ ከተማ ላደረጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተቋማት የስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አመራሩ በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን በመጠቀም ለውጤታማነት መስራት ይጠበቅበታል።

አንድ የሚያደርጉን በርካታ ዕሴቶች አሉን ያሉት አቶ ጥላሁን÷ በአዲስ አስተሳሰብ የብልፅግና ተምሳሌት ክልል ለመመስረት በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ከፍተኛ ተቋምት ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመው÷ የከተማዋ ነዋሪዎችም ለክልሉ አመራሮች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሸን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version