Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ለሕብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ሠራተኛው ለሕብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሐብት ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የአገልጋይነት ቀን እየተከበረ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ባንችአምላክ ገብረማርያም የአገልጋይነት ቀንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች የሚፈቱት አገልግሎትን ለሁሉም ተገልጋይ እኩል ተደራሽ ማድረግ ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

በየደራጀው ያለው አመራርና የመንግሥት ሠራተኛም በተመደበበት የሥራ ቦታ ሁሉ ሕብረተሰቡን በቅንነት እንዲያገለግል ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለሕብረተሰቡ አገልግሎትን በፍትሐዊነት ተደራሽ ማድረግና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ተጠያቂነት ባሰፈነ መንገድ መፍታት እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version