Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ ዛሬ መካሄዱን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የተካሄደው ጉባኤ÷ ገንቢ እንዲሁም መፍትሄን ያማከለ ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ችግር በአስቸኳይ ለመፍታት ያለመ ጉባዔ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡
ቀጣይነት ያለው ሠላም ለመፍጠር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ከሱዳን ሕዝቦች ጋር በትብብር እንሠራለንም ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፡፡
የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version