አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኢትዮጵያ በማዕድን ቁፋሮ የተሰማራው ከፊ ሚኒራል ኩባንያ በ3 ነጥብ 77 ሚሊዮን ፓውንድ የማስፋፋት ዕቅድ እንዳለው አስታወቀ።
በኢትዮዽያ በማዕድን ማውጣት ላይ የተሰማራው ከፊ ሚኒራል የ569 ሚሊየን አዳዲስ አክሲዮኖችን ለነባርና አዲስ ባለ አክሲዮኖች ለመሸጥ በነበረው ዕቅድ ከወጪ በፊት 3 ነጥብ7 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ኢንቨስተሮች የእንግሊዝ ባለሀብቱን ራብ ካፒታል የሚያካትት 236 ሚሊየን አክሲዮኖችን የሚይዝ ነው።
ከፊ ሚኒራል ኩባንያ አጠቃላይ የካፒታል ድርሻ መጠን 12 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆነውን የሚወክል 236 ሚሊዮን አክሲዮኖችን ይይዛል ሲል ማይኒንግ ዊክሊ በድረ ገጹ ማስነበቡን ኢዜአ ዘግቧል።
ራብ ካፒታል የረጅም ጊዜ ባለ ድርሻ እንደሆነ ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን ከ10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የኬፊ አክሲዮኖችን በመያዙ ለድርጅቱ ቦርድ ዳይሬክተር የመሾም መብት አግኝቷል።
የተቀማጭ ክፍያው የተጣራ ወጭ 3ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ያህል ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ መረጃው አትቷል።
በኢትዮጵያ ቱሉ ካፒ ፕሮጀክት በ260 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የፕሮጀክት ገንዘብ ለመመደብ የሚያስችለውን ገንዘብ ለኩባንያው እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

