አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 20 አባል ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን ቋሚ አባል አድርጎ መቀበሉ ይፋ ሆነ።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኒው ደልሂ እየተካሄደ ባለው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ህብረት ቡድኑን መቀላቀሉን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ቋሚ አባል እንዲሆን የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ሁሉም የአባል ሀገራቱ መሪዎች እንደተስማሙበት ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረትን ሊቀመንበር የሆኑትን የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ በቡድን 20 ለህብረቱ የተዘጋጀውን መቀመጫ እንዲይዙ ጋብዘዋል።
ውሳኔው 55 አባል ሀገራት ላሉት አህጉራዊ ተቋም የአፍሪካ ህብረት በተጋባዥ ዓለም አቀፍ ድርጅትነት በቋሚነት መቀመጫ ያስገኘ መሆኑን ዘገባዎች አመልተዋል።