Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፍቷል፡፡

ጳጉሜን 4 ከሸማችነት ወደ አምራችነት በሚል መሪ ስያሜ በከተማ አቀፍ ደረጃ የአምራችነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ መክፈቻ መርሐ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም እንዳሉትም ፥ የዘላቂ ልማታችንና ህልውናችን ቁልፍ የሆነዉ አምራችነት በመሆኑ ከሸማችነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር የሀገርን ኢኮኖሚ መገንባት ይገባል።

ከተማ አስተዳደሩ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ገልጸው ፥ በቀጣይ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ መንግስት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቡዜና አልከድር በበኩላቸው ፥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር በሀገር ምርት በመኩራትና የገበያ ትስስር ማጠናከር ይገባልም ነው ያሉት፡፡

አክለውም ፥ አምራቾች ከጠባቂነት ተላቀው ተወዳዳሪ አምራች መሆን እንዳለባቸውም መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version