Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የእንሰት ድህረ-ምርት ሒደትን ማዘመን የሚያስችሉ ቴከኖሎጂዎችን የማበልጸግ ስራ መጀመሩ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንሰት ተክል ድህረ ምርት ሒደትን የሚያቀላጥፍፉና በአመራረት ሒደት የሚኖረውን የሥራ ጫና የሚቀርፉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ እያስገባ መሆኑን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ።

የእንሰት ተክል ድህረ-ምርት ሒደትን ማዘመን የሚያስችል ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) ÷ የእንሰት ድህረ ምርት ሒደትን የሚያቀላጥፉና በአመራረት ሂደት የሚኖረውን የሥራ ጫና መቅረፍ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም የእንሰት ማብላያ እርሾ በማበልጸግ ብሎም በእንሰት ምርት ላይ እሴት በመጨመር እንደ ኩኪስ፣ ዳቦ፣ ኬክና ሌሎች ምግቦችን መስራት መቻሉን አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው የእንሰት ሰብልን ለማስፋፋት ብሎም ድህረ ምርት ሒደትን ለማዘመን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የትብብር ሥራ መጀመሩን አንስተዋል፡፡

ለዚህም መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version