አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት በጓንጓ ወረዳ ራንች መጠለያ ካምፕ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ወደ ማንዱራ ወረዳ ተመልሰዋል።
ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ 853 የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።
ወረዳው ተፈናቃዮች መደበኛ የእርሻ ስራዎችን እንዲያከናውኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ተገልጿል።
ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት በማስመለሱ ሂደት የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች በትኩረት እየሰሩም ይገኛሉ።
በቀጠናው ሰላምን በማስፈን በሁለቱም ክልሎች በኩል ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ነበሩበት ለማስመለስ በመከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተጠቁሟል።

