Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሲዲሲ አፍሪካ ከፈረንሳይ መንግስት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በህብረተሰብ ጤና ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ጂን ካሴያ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የፈረንሳ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ተፈራርመውታል፡፡

የተደረገው ስምምነት የአፍሪካ ሲዲሲ የተጠናከረ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ያስችለዋል የተባለ ሲሆን ይህም በአህጉሪቱ ያለውን የጤና ስርዓት ለማሻሻል አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሲዲሲን አቅም ማጠናከር፣ የህዝብ ጤና ተቋማትን መደገፍ ፣የበሽታ ክትትል እና የአደጋ ምላሽ አቅምን ማሳደግ እንዲሁም የክትባት እና የምርመራ አቅሞችን ማጎልበት የስምምነቱ ትኩረቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ፈረንሳይ ቀደም ሲል በአፍሪካ አህጉር የጤና ስርዓት እንዲጎልበት ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን የባዮ ስፔክትረም መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version