አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ9 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ይፋ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ ኢትዮጵያ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማሥተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በኩል የሚሰራጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ አምባሳደር ኒኮላ ብሬናን ÷የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚያጋጥሙ ሰብዓዊ ችግሮችን ለማቃለል ያስችላል ብለዋል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፉ ከፈረንጆቹ 2023 እስከ 2025 ተግባራዊ እንደሚደረግም በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!