አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እየተሰራ መሆኑ ተመለከተ።
በክልሉ የቤንች ሸኮ፣ የሸካ እና የምዕራብ ኦሞ ዞኖች ኩታ ገጠም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ሀብታሙ ዓለሙ እንደገለፁት÷ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የክልሉ መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመስራቱ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በ2015 ዓ.ም በሠላምና ፀጥታ ላይ በቅንጅት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው÷ በተያዘው የበጀት ዓመትም በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የሶስቱም ዞኖች የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የክልሉ የፖሊስ እና በአካባቢው ያሉ የፌደራል ፖሊስ አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!