Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 29 ጀምሮ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፊታችን መስከረም 29 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎችና ከክልሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በክልሉ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማስቀጠል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ተናግረዋል፡፡

ፈተናውን በሶስት ዙር ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመው÷የመጀመሪያው ዙር ፈተና (የ2012 ዓ.ም) ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 8 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንደሚከናወን መገለጹንም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version