Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ከ1ሺህ በላይ የሞባይል ስልኮች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ህጋዊ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 1ሺህ 812 ቴክኖ ሞባይል ስልኮች መርካቶ ከተራገፉ በኋላ ተይዘዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባከናወነው ተግባር ዛሬ ንጋት ላይ በመዲናዋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል አካባቢ ሞባይል ስልኮቹ በ6 ካርቶን ታሽገው ከመኪና እንደተራገፉ መያዛቸው ተገልጿል፡፡

በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አለው ተብሎ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Exit mobile version