አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ አደሩ በግል እና በቡድን ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን እንዲያገኝ የሚያስችሉ የግብርና ሜካናይዜሽን ማዕከላት በሁሉም ክልሎች እየተገነቡ ነው።
የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
በነበራቸው ቆይታም ለአርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉ 10 የሜካናይዜሽን ማዕከላት እየተቋቋሙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አራቱ ማዕከላት ወደ ሥራ ገብተዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ÷ ቀሪዎቹ በተያዘው በጀት ዓመት እንዲጠናቀቁ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ማዕከላቱ ከዚህ ቀደም ለዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎች ጥገና ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ባለሙያዎችን ለማሰልጠን የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
የዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን መለዋወጫ በማቅረብ ረገድም ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ እንደሆኑ ነው የተናገሩት።
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!