Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ከ15 ሺህ በላይ ወጣት አስተባባሪዎች እየተዘጋጁ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ከ15 ሺህ በላይ ልምድ ያላቸው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ፡፡

የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ይሁነኝ መሀመድ በአዲስ አበባ የሚከበሩትን የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበር ማኅበሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም በማስተባበር ልምድ ያላቸው ከ15 ሺህ በላይ ወጣቶች ከሰላምና ጸጥታ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ጋር በቅንጅት እየሠራን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወጣቶቹ በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ከማስተባበር ባለፈ እንግዶችን በአግባቡ የማስተናገድ ሥራ እንደሚሰሩም አመላክተዋል፡፡

በዓላቱ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ የመዲናዋ ወጣቶች በየአካባቢያቸው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰሩ ማኅበሩ ጥሪ አቀርቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version