Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ የተስተጓጎለውን የልማት ስራ ለማካካስ እየተሠራ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር የተስተጓጎለውን የልማት ስራ ለማካካስ የተቀናጀ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ የተፈጠረውን የሰላም ችግር ተከትሎ የግብርናው ዘርፍ ከእርሻ ስራ እስከ ግብዓት አቅርቦት ሲፈተን መቆየቱን የቢሮው ኃላፊ ድረስ ሣኅሉ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎም በበርካታ አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የግብርና ልማት ባለሙያዎች ከአርሶ አደሩ ጋር በመሆን እየሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ርጥበት በሚቀጥልባቸው አካባቢዎች የሚለሙ ሰብሎች የማሳ ዝግጅትና የበጋ መስኖ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው÷ የሰብሉን እድገት ጤናማና ምርታማ ለማድረግ የዩሪያ ማዳበሪያ በበቂ ሁኔታ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው ብለዋል፡፡

በቀሪዎቹ ርጥበታማ ወቅቶች ለሚዘሩ ሰብሎች የሚያገለግል የግብዓት አቅርቦት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ወደ ክልሉ እየገባ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version