Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ከ11 ሺህ 581 ተማሪዎች የሀገር አቀፍ  ፈተናቸውን ለመውሰድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎቹን ለማስፈተን ዝግጅት ማደረጉን አስታውቋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች÷ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ማጠናቀቅ አለመቻላቸውን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂና ሲቪክስ የትምህርት አይነቶችን ብሄራዊ  ፈተና ይወስዳሉ  መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version