Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአማርኛ ቋንቋ መሰጠት መጀመሩ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያ፣ ባህላዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያጠናክራል ነው የተባለው፡፡

ተማሪዎቹ በበኩላቸው አማርኛ ቋንቋ ከማወቅ በተጨማሪ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ህዝቡን እና የኢትዮጵያን ባህል ማየት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ የአፍሪካ ቋንቋዎችን የመማር ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ከአማርኛ በተጨማሪ በአፍሪካ ከፍተኛ ተናጋሪ ያለው የስዋሂሊ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት መጀመሩን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version