Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሥነ-ምግባር ግድፈት መንግስት ሊያጣው የነበረ ከ268 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥነ-ምግባር ግድፈትና በአሰራር ጥሰት መንግስት ሊያጣው የነበረ ከ268 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

በኮሚሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ አዘዘው ጫኔ÷ በኮሚሽኑ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች እንቅፋት እንዳይገጥማቸውና ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከምንጩ ለማድረቅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሥነ-ምግባር መከታተያ ስርዓት ስራውን ሳይንሳዊ ወደሆነ የተቋማዊ ስጋትና ስራ አመራር ስርዓት ማሸጋገሩን አንስተዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመትም የተቋሙን ጤንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ሥነ-ምግባር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም አበበ በበኩላቸው÷ ኮሚሽኑ ተልእኮውን በአግባቡ እንዳይወጣ ሌብነትና ብልሹ ስነ-ምግባር ቀዳሚ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት በሥነ-ምግባር ግድፈትና በአሰራር ጥሰት መንግስት ሊያጣው የነበረ 268 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ማዳን መቻሉን አስታውሰዋል።

በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የሥነ-ምግባር ጥሰቶች 417 አመራሮችና ሰራተኞች ላይ የዲሲፕሊንና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version