Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የግሪሳ ወፍን ለመቆጣጠር በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እንደሚጀመር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የግሪሳ ወፍን ለመቆጣጠር የሚያስችል በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት በመጭዎቹ ሦስት ቀናት እንደሚጀመር ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ የእፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አሥፈፃሚ በላይነህ ንጉሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የግሪሳ ወፍ መንጋው በተከሰተበት አካባቢ የኬሚካል ርጭት ለማድረግ ከሚመለከተው አካል ጋር ሥምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

የቅድመ ዝግጅትና የኬሚካል አቅርቦት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንም ነው የተናገሩት።

ሆኖም ሁሉንም አካባቢዎች በአውሮፕላን ርጭት ብቻ መድረስ ስለማይቻል አርሶ አደሩ በባሕላዊ መንገድም የመከላከል ስራ እንዲሰራ መክረዋል።

አቶ በላይነህ አክለውም አርሶ አደሩ ማማዎች በመሥራት፣ የመንጋዎችን መራቢያ ቦታዎች በማፈራረስ እና ሰው መሳይ ምሥሎችን በመሥራት መከላከል እንዳለበት አመልክተዋል።

በቅርቡም በምሥራቅ ሐረርጌ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ በኬሚካል ርጭት መቆጣጠር እንደተቻለም አስረድተዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version