አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ባሕል ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ ዝግጅቱን በፑሽኪን አዳራሽ አቀረበ፡፡
ሚኒስቴሩ ባሕላዊና ሐይማኖታዊ እሴቶች የጎሉበትን መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ፑሽኪን አዳራሽ ያሰናዳው ÷ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት መምሪያ እና በኢትዮጵያ ከሩሲያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነው፡፡
ዝግጅቱ በሩሲያ ሰርጊየስ ላቭራ የሥላሴዎች መዘምራን እና በሞስኮ የሥነ-መለኮት ተማሪዎች ሐይማኖታዊ ዝማሬ የደመቀ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረኪን ÷ መርሐ – ግብሩ የኢትዮ-ሩሲያን የባሕል እና የሐይማኖት እሴቶች እንዲሁም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እና ታሪክ ለማስተዋወቅ እና ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የሩሲያ ኤምባሲ በሀገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊና የቆየ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዙ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ቤተ ክርስቲያናት ግንኙነት ክፍል የክርስቲያኖች ግንኙነት ዋና ፀሐፊ ሄይሮሞንክ ስቴፋን ÷ ዝግጅቱ የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ጅምር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!