Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመውሊድ በዓል ሲከበር የነብዩ መሐመድን ደግ ሥራዎች በመተግበር ሊሆን ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመውሊድ በዓል ሲከበር የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ደግ ሥራዎቻቸውንና እዝነቶችን ተግባራዊ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

1 ሺህ 498 ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጂድ ነገ እንደሚከበር የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባል ሼህ አብዱልሃሚድ አሕመድ እንዳሉት÷ ሕዝበ ሙሰሊሙ የነብዩ መሐመድን ልደት የሚያከብረው የእሳቸውን የደግነት ሥራዎች ተግባራዊ ለማድረግና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡

ነገ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ የቅደመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውን አስታውሰው÷ በዛሬው ዕለትም በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ የማጽዳትና የማስተካከል ስራ ተከናውኗል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version