Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነፃ የትምህርት ዕድል የተመቻቸላቸው ተማሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነፃ የትምህርት ዕድል የተመቻቸላቸው ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

273 የሚሆኑ ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቅድመ ምረቃ መርሃ-ግብር ነፃ የትምህርት ዕድል እንደተመቻቸላቸው ይታወሳል፡፡

ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያቀኑት እነዚህ ተማሪዎች በአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና ሰራተኞችም ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተማሪዎቹ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኙ አሥር ዩኒቨርሲቲዎች የቀረበላቸውን የመግቢያ ፈተና ያለፉ መሆናቸውም ተገልጿል።

ነፃ የትምህርት ዕድሉ በበኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል እየጎለበተ የመጣው ወዳጅነትና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ከፍ ያለ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የነፃ የትምህርት ዕድሉ ተጠቃሚዎቹም ይህንን እድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ ለዚህም ለኢትዮጵያና ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version