Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመኸር ወቅት 513 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመኸር ወቅት 17 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር በማልማት 513 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ፣ ሐረሪ ክልሎች እና በድሬዳዋ አስተዳደር 17 ሚሊየን 390 ሺህ 818 ሔክታር ለማረስ መታቀዱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

እስካሁንም 14 ሚሊየን 137 ሺህ 156 ሄክታር በባሕላዊ እንዲሁም በዘመናዊ የእርሻ አስተራረስ ዘዴ 3 ሚሊየን 960 ሺህ 990 ሄክታር መታረሱን አረጋግጧል፡፡

ከታረሰው መሬትም 16 ሚሊየን 578 ሺህ 415 ሄክታር በዘር ተሸፍኗል ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

በዘር ከተሸፈነው መሬት መካከል 8 ሚሊየን 280 ሺህ 741 ሄክታር በኩታ ገጠም እርሻ ለምቶ በዘር የተሸፈነ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version