Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ197 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከመስከረም 4 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 197 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡

ከዚህ ውስጥ 92 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች ሲሆኑ÷ 105 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገሮች ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ድሬድዋና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ ነው የተባለው፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ ድርጊትን ለመግታት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version