Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።

ጄኔራል መኮንኑ የተሾሙት በምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የዝውውር መመሪያ መሠረት ሲሆን የአዲሱ አመራር መተካት ድርጅቱ ሚናውን በትክክለኛው አቅጣጫ ወደፊት ለማራመድ የሚችልበት ትልቅ ዕድል ይኖረዋል ተብሏል።

ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው ለመጭዎቹ ሦስት ዓመታት የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ዳይሬክተር ሆነው ያገለግላሉ።

ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው ከሶስት ቀን በፊት ናይሮቢ ኬንያ በሚገኘው የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ተገኝተው ሃላፊነቱን መረከባቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version